ድምፃዊት ፀደኒያ ስለኢንተርቪዥን ውድድር ምን አለች?

Date:

ድምፃዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ የውድድሩ ተሳታፊዎችን በተመለከተ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጠችው አስተያየት፣ አፍሪካውያን ድምፃቸውንና ታሪካቸውን በዓለም መድረክ፣ በአዲስ ታዳሚ፣ በአዲስ እድልና በአዲስ ፈተና ፊት የሚያሳዩበት ነው ብላለች፡፡

በተወሰኑ አርቲስቶች የተገደበውን የዓለም አቀፍ መድረክ ተሳትፎ ለማስፋትና ተደራሽነተን ለማሳደግ እንደ ኢንተርቪዥን ያሉ ውድድሮች እድል ይሰጣሉ ስትል ገልጻለች፡፡

” የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍተኛ አቅም ማሳየትና ቀጣይ የስራ ህይወታቸውን ድንበር ተሻጋሪ አድርገው ትስስርን ለመገንባት ያስችላቸዋል፡፡ …. በተለይም ወጣቶች ከሀገር ውስጡ ባሻገር ማሰብ እንዲችሉ እድል ይሰጣቸዋል፡፡” በማለት የአፊሪማ እና ኮራ የሙዚቃ ሽልማቶች ባለቤቷ ደምፃዊት ፀደኒያ የኢንተርቪዥን ተሳትፎ አበርክቶን አስረድታለች፡፡

ኢንተርቪዝን ከሙዚቃ ውድድር ባሻገር የትስስር ድልድይን መገንቢያ፣ የዲፕሎማሲ መስክን ማስፊያ፣ ለትብብር በር ከፋችና አካታችነትን የሚያሳድግ መሆኑንም እውቋ ድምፃዊት ገልፃለች፡፡

“ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው። ስለ አሜሪካውያን፣ ስለ ብሪቲሽ ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ባልተገደበና ሁሉንም አካታች ሆኖ ተደራሽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ኢንተርቪዥን ከሩስያ ባሻገር ያሉ አርቲስቶችን ፣ ከእስያ የተሻገሩ ሀገራትን ያሳተፈ ነው፤ በዚሀም ነው እኔ የወደድኩት፡፡” ስትል ተናግራለች።

Sputnik Africa-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...