ድምፃዊ ዳዊት መለሰ ምን አለ?

Date:

★ሚዲያ ላይ ቀርቤ አላውቅም። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አንተ ጋር የቀረብኩት።

★ ሙዚቃ የክፉ ቀን ባለውለታዬ ብቻ ሳትሆን አሁንም እያኖረችኝ ነው።

★ አባቴና እናቴ ብሔራዊ ባንክ ነበር የሚሰሩት። አባቴ
ሙዚቃና ፊልም ይወዳል። እሁድ እሁድ ሲኒማ ይዞኝ
ይገባ ነበር።

★ ሸክላ ማጫወቻ ነበረን። አዳዲስ ዘፈኖች ሲወጡ አባቴ
እየገዛ ይመጣ ነበር።

★ ድሮ ልጅ እያለሁ ሙዚቃ እወድ ነበር።
ጓደኛዬ የከፍተኛ 18 ኪቦርድ ተጫዋች ነበር። ቤተሰቦቹ
የሙዚቃ መሣሪያ ይሸጡ ነበር። ጓደኛዬ የሆነ ቀን እስኪ
ዝፈን አለኝ በስሜት ገባሁበት። ስሙ ሚሊዮን ሞገስ ይባል ነበር። አሁን በህይወት የለም።

★ ከፍተኛ 18 ስገባ ድራመሩ ጠፋ ተባለ። ቀንና ማታ አጥንቼ ድራም ይዤ እዘፍን ነበር።

★ እንግሊዝኛ ስለምዘፍን ከሌሎቹ ለየት ብዬ ነበር የቀረብኩት።

★ ፋሲካ ዲሚትሪ ቤዝ ጊታሪስትና ዘፋኝ ነበር።

★ በጊዜው ደናሽም ነበርኩኝ። ዴይ ፓርቲ ላይም እንደዲጄም እሆን ነበር።

★ አብሮ አደጎቼ በሙሉ መሣይ ብለው ነው የሚጠሩኝ።

★ ቴዲ አፍሮ የቀድሞ ፍቅረኛዬን ያውቃት ነበር። አሜሪካ ሀገር ሲመጣ ደህና ነች ወይ? ሲለኝ አዎ ደህና ነች ሞክረን ነበር አልሆነም አልሰራም አልኩት።

እህል_ውሃ የሚለውን ዘፈን ሰርቶ ሰጠኝ።

ቴዲን የማደንቀው ትልቅ ጭንቅላት ያለው ልጅ ነው።
በዜማም በግጥምም የበሰለ ልጅ ነው።
ከራሴ ህይወት ጋር የሚገናኝ ዘፈን የዘፈንኩት #እህል_ውሃ
የተሰኘውን ዘፈን ነው።

★ ቴዲ #ውቤ_ከረሜላ የሚለውን ዘፈን ሰጠኝ።

★የኤክስፕረስ ባንድ ሲቋቋም ለ 1 ዓመት የባንዱ ሊደር ነበርኩኝ።

★ እጃችሁን ወደላይ ወደላይ ከፍ አድርጉት በሚለው ዘፈኔ
ዴቭ አሰረቅከን የሚሉኝ ብዙ ሰዎች አሉ።

★ ሀገርፍቅር ቴአትር ቤት ቋሚ ተቀጣሪ አልነበርኩም።

★ የአለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ተመርጬ ሄጃለሁ።

★ አበበ መለሰ ጥሩ ወዳጄ ነው። ባለውለታዬ ነው።

★ የግርማ በየነን ሴት አላምንም እና የነዋይ ደበበን ገዳም
ሰርቼ ለኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ለጋሽ ተሼ አሰሙት።

★ ከስንት ጊዜ በኋላ ጋሽ ተሼ ጠርቶን እንድትሰሩ እፈልጋለሁ አለን።

★ የመጀመሪያው ካሴቴ ሲወጣ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ከሀገር የወጣበት ጊዜ ነበር።
በሳምንቱ ደግሞ ፍንዳታ ተከስቶ ካሴቴ ብዙም አልተደመጠም። ድሬዳዋ ግን ብዙ ተደምጧል።

ነጋ_ነጋ የምትለው ዘፈኔ ግን ጎልታ ወጣች።

★ ድሬዳዋ ላይ እየዘፈንኩኝ አንዱ ከሩቅ ተንደርድሮ መጥቶ
ክንዴን የነከሰኝን ገጠመኝ አልረሳውም።

★ ናይት ክለብ ውስጥ በአብዛኛው የምዘፍነው

ይበራል_ልቤ የሚለውን ዘፈን ነው።

ድሬዳዋ #አልቻልኩምን ስራልኝ አሉኝ።
ማታ ገብቼ ስዘፍነው ሕዝቡ ከእኔ እኩል ነው አብሮኝ
የዘፈነው። ዘፈኑን 4 ጊዜ አስደግመውኛል።

★ ከአስቴር አወቀ ጋር ብዙ ኮንሠርት ሰርተናል።
ከሷ ጋር በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

★ ኢትዮጵያ ላይ ናይት ክለብ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ድረስ እሰራ ነበር።

★ አሜሪካ ሀገር ናይት ክለብ በሳምንት 5 ቀን እሰራ ነበር።
እረፍቴ ማክሰኞ ብቻ ነበር።

★ ከአሜሪካ ሀገር ስመጣ ትልቅ የድንጋይ መፍጫ ገዛሁኝ።
ነገሮች ግን እንደፈለግሁት አልሄዱም።
በጣም ብዙ ብር ነው የከሰርኩት። የነበረኝን ሁሉ ጨርሼ
በሙዚቃ እንደአዲስ ነው የጀመርኩት። ሙዚቃ ባይኖር
ኖሮ ምን እንደምሆን አላውቅም ነበር።
እግዚአብሔር ሁለተኛ ዕድል ሰጥቶኛል።
በሙዚቃ ተነስቼ ከ22 ዓመት በኋላ በድሮ ዘፈኖቼ እየሰራሁ ነው።

★ በዓረብኛ ፣ በእንግሊዝኛ ፣ በአደርኛ ፣ በጣሊያንኛና በጉራግኛ ዘፍኛለሁ።

★ በኮረና ጊዜ ከጓደኞቼ ጋር ሄጄ ደም ሰጥተናል።

★ ሶሻል ሚዲያ መጠቀም የጀመርኩት የዛሬ 7 ወር ነው።

★ ትሬንዱ ተቀይሯል። ሰው ጋር እንዲያደርሱልኝ እንጂ
ሙዚቃዬን ይገመግማሉ ብዬ አይደለም ቲክቶከሮቹን የጋበዝኳቸው።

★ ከልጆቼ እናት ባለቤቴ ጋር ስንገናኝ ዘፈኖቼን አታውቃቸውም። እኔነቴን ወዳኝ ነው የቀረበችኝ።

★ በራሴ ዘፈን ከባለቤቴ ጋር ደንሼ አውቃለሁ።

★ ኩኩ የዘፈነችው #ወይ_ጊዜ የሚለው ዘፈን ለእኔ ነበር የተሰራው።

★#መውደዴንወድጄዋለሁ የተሰኘው ዘፈን ለሸዋንዳኝ ነበር የተሰራው። ሸዋንዳኝ #እህልውሃ የተሰኘውን የኔን ዘፈን ይወደዋል።

★ #ቁንጅና የተሰኘው ዘፈኔን አለምፀሐይ ወዳጆ የፃፈችው የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።
ዘፈኑን የፃፈው ዮናስ ሙላቱ የተባለ ኪቦርድ ተጫዋች አለ።
ቁንጅና እና ብቻሽን የተሰኘ ሁለት ዘፈን ሰጠኝ።
አለምፀሐይ የፃፈችው #ፍረጂኝ የተሰኘውን ዘፈን ነው።

★ ታማኝ በየነ አሜሪካ ሀገር ዋና አሰባሳቢያችን ነበር።
ሐሙስ ሐሙስ አሁንም ድረስ እንሰባሰባለን።

★ ባለቤቴና ልጆቼ አሜሪካ ሀገር ነው የሚኖሩት። እኔ እየተመላለስኩኝ ነው የምሰራው።

★በልጆቼ ስም BB’S የሚል ላውኝጅ ከፍቼ ነበር።

★ ልጆቼ ሙዚቃ ይወዳሉ።

★ የአዲሱ አልበሜ ምርቃት ዲሴምፐር 13 በቨርጂኒያ ይካሄዳል።

★ አዲሱ አልበሜን ከበፊቱ ከፍ ማለቱን ወይም ዝቅ ማለቱን
ለአድማጮች ትቼዋለሁ።

★ አልበሜን ስሰራ ብዙ ሰው ከአጠገቤ ነበር። ብዙ የተባበሩኝ ሰዎችን እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
በጣም አመሰግናለሁ።

Dawit Mellesse ለሰጠኸን የማይጠገቡ ዘፈኖችህ የ90ዎቹን ምርጥ ጊዜ ስላሳመርክልን እናመሰግናለን።
ለአዲሱ አልበምህ መልካም ዕድል !

አክባሪህና አድናቂህ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...