ከተለያዩ የገቢ አማራጮች ከ33 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰ

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት አራት ወራት ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች በአጠቃላይ 33.65 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ፡፡

ይህም በዕቅድ ለመሰብሰብ ከተያዘው 33.72 ቢሊዮን ብር አንፃር 97 ከመቶ አፈፃፀም ያለው መሆኑን ጨምረው ጠቁመዋል፡፡

ዋና ስራ አሰፈፃሚው በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ከኢነርጂ ሽያጭ ብቻ 22.21 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቁመው፤ ከዕቅዱ አንፃር 99 ከመቶ አፈፃፀም ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢንጅነር ጌቱ አክለውም ባለፉት አራት ወራት 153 ሺህ 973 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መደረጉን ጠቅሰዋል ።

በተቋማችን የዲጂታል ክፍያ ስርአትን ለማጠናከር እየተደረገ ባለው ጥረት በጥቅምት ወር በኢ-ፔይምነት ክፍያ የፈፀሙት ደንበኞች ቁጥር 95 በመቶ መድረሱንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...