በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል ገጣሚና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ በሥራዎቿና በሕይወቷ ዙሪያ ልምዷን ታጋራለች፡፡
በዕለቱ ስለገጣሚነቷ፣ ስለሠዓሊነቷ፣ በሶማሊያ ሐዋይ የ10 ዓመታት የእስር ቤት ቆይታዋ፣ በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ በተማሪነትም በመምህርነትም ስላሳለፈቻቸው ዓመታት ታወጋናለች፡፡
ዝግጅቱ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 19፣ 2017 ከ8 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይቀርባል፡፡
ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ነው፡፡
የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል በዝግጅቱ እንዲታደሙ ግበዣውን ያቀርባል፡፡
የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡
