ጉግል በክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ ላይ ለተከሰተዉ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ማስተካከያ ለቀቀ

Date:

ጉግል በክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ #browser ላይ የታዩና ቀድሞ ያልተለዩ #zero_day ተጋላጭነቶችን የሚቀርፍ የደህንነት ማሻሻያዎችን ለቀቀ፡፡

ይህ ክፍተት (CVE-2025-10585) አደገኛ ከሚባሉ ክፍተቶች መካከል የሚመደብ እንደሆነ ጎግል ገልጿል፡፡ እንዲህ አይነት ቀድሞ ያልተለዩ (zero-day) ተጋላጭነቶች በፈረንጆቹ 2025 ብቻ በክሮም ላይ ለስድስተኛ ጊዜ እንደተከሰቱ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ አደጋ ስጋት ለመጠበቅ የጎግል ክሮም የመረጃ ማፈላልጊያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ስሪት መሰረት ማዘመን እንደሚያስፈልግ ጉግል አሳስቧል፡፡

ዊንዶውስ #Windows እና ማክ ኦኤስ #macOS ምርት ተጠቃሚዎች ወደ ክሮም ስሪት: 140.0.7339.185/.186 ማዘመን እንዲሁም የሊነክስ #Linux ምርት ተጠቃሚዎች ደግሞ ወደ ክሮም ስሪት፡140.0.7339.185 ማዘመን ይጠበቅባቸዋል።

በተጨማሪም እንደ #Microsoft_Edge፣ #Brave፣ #Opera እና #Vivaldi ያሉ ሌሎች በክሮሚየም #Chromium ላይ ለተመሰረቱ የመረጃ ማፈላልጊያዎች ላይ የክፍተት መሙያ መለቀቁንና ተጠቃሚዎች በፍጥነት እንዲያዘመኑም ኩባንያው መክሯል።

ተገልጋዮች ወደ ክሮም የመረጃ ማፈላልጊያ በመሄድ ክሮምን በማዘመን ሊደርስ ከሚችል የጥቃት ተገላጭነት ራስን መጠበቅ አንደሚገባ መረጃውን ያጋራው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባጋራው መረጃ አሳስቧል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...