ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሩሲያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የምታደርግባቸውን ዘርፎች እንድታሰፋ ጥሪ አቀረቡ

Date:



የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ሥራ አስፈፃሚ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን እና ከሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭን ጋር ተገናኝተው በስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

“ሩሲያ በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አድናቆት አለን፡፡ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና በማዕድን ልማት እንዲሁም በማዳበሪያ ምርት፣ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና የኒውክሌር እና ታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በኃይል መሠረተ ልማት፤ ለሩሲያ ኢንቨስትመንት እና የጋራ ትብብር ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡  

▫️ እነዚህ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች በዘላቂ ልማት፣ በቀጣናዊ ደህንነት እና በጋራ ብልጽግና ላይ በማተኮር የኢትዮጵያ-ሩሲያ አጋርነትን ወደ አዲስ የስትራቴጂካዊ ትብብር ደረጃ ለማሳደግ ማሳያ ናቸው ሲል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...