ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ዛሬ ወንድሜን አሊኮ ዳንጎቴን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።
በውይይታቸውም ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስችሉ ስልታዊ የኢንቨስትመን መስኮች ላይ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
