ዓለም በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች የታገዙ ጦርነቶች ሁሉንም ነገር የሚያሳጡ እና ሰዎች በጭካኔ እንዲሞቱ የሚያደርጉ መሆናቸውን የፖፕ ሊዮ 17ኛ ገለጹ።
ጦርነትን መምረጥ መሸነፍ ነው ያሉት ፖፕ ሊዮ፥ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ሕግን ማክበር፣ ኃላፊነት መውሰድና መተግበር ይበጃል ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ሕግ እና ሰብዓዊ ክብር እንዲጠበቅ የሚመለከታቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካላት፤ በኃላፊነት ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጡም ፖፕ ፍራንሲስ ይጥሩ እንደነበር አስታውሰዋል።
“ጦርነትን መምረጥ ሽንፈት ነው በሰላም የምናጣው ነገር የለም”።
“ምርጫችን ጦርነት ከሆነ ግን ሁሉንም ነገር እናጣለን” የሚለው የፖፕ ፒውስ 12ኛ አስተሳሰብ፤ አሁን ላለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ መድኃኒት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፖፕ ሊዮ ይህን ያሉት በእስራኤልና በኢራን መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ነው።
