በነባር እና አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሴቶች ምቹ የሆኑ ክፍሎችን ለማካተት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

Date:

ሴት ተማሪዎች  የወር አበባ ሲያጋጥማቸው ከትምህርት ቤት የመቅረት እና ከህብረተሰቡ የመገለል ሁኔታዎች አሁንም ድረስ እንደሚስተዋል ይነገራል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የገለፁት በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ምህረተክርስቶስ ታምሩ ናቸው፡፡

ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ወቅት ትኩረት አድርገው ትምህርታቸውን መከታተል እንደማይችሉ እና የግንዛቤ ክፍተት በመኖሩም መገለል እንደሚደርስባቸው በመጥቀስ ይህንን ለመፍታት ነባር ትምህርት ቤቶች ባላቸው ቦታ የንፅህና መጠበቂያ መቀየሪያ እና ማረፊያ ክፍል እንዲያዘጋጁ እየተደረገ መሆኑ ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም አዳዲስ ይገነባሉ ተብሎ በተዘጋጁ የትምህርት ቤት ፕላን ውስጥም ለሴቶች ለብቻ የሚገነቡ ክፍሎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ለተማሪዎች ምቹ የሆነ አካባቢን እና የንፅህና መጠበቂያን ማቅረብ 36 ፐርሰንት የትምህርት ክትትልን የሚጨምር በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አሁንም ድረስ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍልም ሆነ በከተሞች በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እስከ አራት ቀን የሚቀሩ ሰቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

menahriaFm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...