የዓለም የመቶ ሜትር ርቀት ባለድል ኬሪ ሪቻርድሰን ከፍቅረኛዋ ጋር በፈጠረችው ጸብ እና ጥቃት ስላደረሰችበት ይቅርታ ጠይቃለች።
አትሌቷ በሲያትል አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍቅረኛዋ ክሪስቲያን ኮልማን ጋር በመጋጨት ጥቃት በማድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ለአንድ ቀን ታስራለች።
የኤርፖርት ደህንነቶች አትሌት ሪቻርድሰን እጇ በገባላት ቁሳቁስ ሁሉ በመወርወር ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ቢያውላትም ፍቅረኛዋ ክስ ባለመመስረቱ ልትፈታ ችላለች።
አሜሪካዊቷ አትሌት በኢንስታግራም ገጿ እንደርሷ ሁሉ አትሌት የሆነው የፍቅር ጓደኛዋን ይቅርታ ጠይቃለች።
አትሌት ሪቻርድሰን በ2023 በቡዳፔስት በተደረገው የአለም ሻምፒዮና በ100 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ስትሆን፤ በፓሪስ ኦሎምፒክ ደግሞ የብር ሜዳሊያ ለሃገሯ አስገኝታለች።
NBC Ethiopia
