ፎቴን ተስፋይ በባርሴሎና ማራቶን ታሪክ ሰራች

Date:

እሁድ መጋቢት 6 2018 ዓ.ም በተካሄደው የባርሴሎና ማራቶን አትሌት ፎቶን ተስፋይ በታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አስገራሚ ድል ተጎናፅፋለች።

ኢትዮጵያዊቷ ጀግኒት ፎቴን ተስፋይ በሩጫ ህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በሮጠችው የማራቶን ውድድር 2:10:53 በሆነ ሰዓት በዓለም የረጅም ርቀት ታሪክ ሁለተኛዋ ፈጣን አትሌት በመሆን ስሟን በቀዳሚነት አስፍራለች።

የ28 ዓመቷ ፎቴን ውድድሩን ስትጀምር በዓለም በግማሽ ማራቶን ታሪክ ሦስተኛዋ ፈጣን አትሌት ነበረች፤ ውድድሩን ስታጠናቅቅ ግን ያንን ስኬት በእጥፍ ርቀት በማሻሻል ከዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን በአንድ ደቂቃ ባነሰ ልዩነት ውስጥ ሆና አጠናቃለች። አትሌቷ ውድድሩን ያሸነፈችው ሁለተኛ ሆና ካጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ጆአን ጄፕኮስጌ ኪፕሊሞ በስምንት ደቂቃ ቀድማ በመግባት ነው።

በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ 7ኛ እንዲሁም በቶኪዮ 25 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር 8ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ፎቴን፣ የመጀመሪያ የማራቶን ጉዞዋን በባርሴሎና ስትጀምር ሁለት ወንድ አሯሯጮችን በመከተል የመጀመሪያውን 10 ኪሎ ሜትር በ31:05 አጠናቃለች።

አሯሯጮቹ ፍጥነታቸውን በመጨመር ግማሹን ርቀት (21 ኪ.ሜ) በ1:05:05 እንዲያልፉ ያደረጉ ሲሆን፣ በ30ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደግሞ 1:32:00 አስመዝግበዋል።

የፎቴን ግብ ሩት ቼፕንጌቲች በ2024 በቺካጎ ያስመዘገበችውን 2:09:56 የዓለም ክብረ ወሰን መስበር ነበር። 40ኛውን ኪሎ ሜትር በ2:03:31 ስታልፍም ከፍተኛ ቁርጠኝነት ይታይባት ነበር። ምንም እንኳን በዚህ ውድድር ከ2:10 በታች መግባት ባትችልም በታሪክ ፈጣኑን የሴቶች ማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎ (Debut) የኢትዮጵያ አዲስ ክብረ ወሰን እና በዓለም ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች።

ፎቴን በውድድሩ ማብቂያ ላይ በአስተርጓሚ አስተያየቷን ስትሰጥ “ዛሬ ድንቅ ነበር — እንደጠበቅኩት የዓለም ሪከርድን ባልሰብርም ውጤቱ ግን ጥሩ ነው። ዕቅዴ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ነበር፤ ነገር ግን ዛሬ ከፍተኛ ንፋስ ስለነበረ በመጨረሻው የውድድሩ ምዕራፍ ባሰብኩት ልክ ወደፊት መግፋት አልቻልኩም። ዛሬ ባይሳካልኝም በሚቀጥለው ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰኑን ለመስበር እሞክራለሁ” ብላለች።

በውድድሩ ጄፕኮስጌ ኪፕሊሞ በ2:18:42 ሁለተኛ ስትሆን፣ ኢትዮጵያዊቷ ዘይነባ ይመር በ2:18:49 ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ምስጋናው ታደሰ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...