ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽንስ (PSS) እና ማስተርካርድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የዲጂታል ክፍያ ማረጋገጫ ስርዓት ይፋ አደረጉ።
በEMV 3-D Secure (3DS) ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተው ይህ አዲስ አገልግሎት፣ እየጨመረ የመጣውን የኦንላይን ክፍያ ማጭበርበር ስጋት ለመቀነስ እና የኢ-ኮሜርስ ንግድን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የPSS ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አምሃ ታደሰ፣ ይህ ስርዓት ለሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። የማስተርካርድ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸህሪያር አሊ በበኩላቸው፣ አገልግሎቱ የዲጂታል ሽግግርን ከማፋጠኑም በላይ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር እንደሚረዳ ተናግረዋል።
አዲሱ ስርዓት ለነጋዴዎች፣ ለባንኮች፣ ለፊንቴክ ኩባንያዎች እና ለደንበኞች ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥም ተጠቅሷል።
CapitalNews
