1ሺህ 136 እስረኞችን በዋስ እንዲፈቱ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ

Date:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን  የስድስት ወር የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ ሰጥቷል።

ባለፉት ስድስት ወራት በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ መሻሻል መኖሩን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ብርሀኑ አዴሎ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከፌደራል እና ከክልል መንግስታት  ጋር  ባደረገዉ ዉይይቶች  1ሺ 136  የህግ ታራሚዎች ጉዳያቸው ተገምግሞ በዋስ እንዲፈቱ ማድረግ ተችሏል ሲል አስታውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ 119ኙን ለማስፈታት ሙከራ ተደርጎ ተጠርጥረው የተያዙበት ምክንያት በዋስ እንዲፈቱ ለማድረግ አስቻይ ባለመሆኑ፤የፍርድ ቀጠሯቸውን እንዲከታተሉ መወሰኑ ተገልፃል።

በማረሚያ ቤት የእለት ምግብ ፍጆታ ላይ ተደጋጋሚ  ቅሬታ ሲነሳ ቢቆይም በተወሰነ መንገድ በአንዳንድ የማረሚያ ቤቶች ችግሩን ለመቅረፍ መሞከሩን ቢገልፁም ፤ ነገር ግን አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።

ሌሎች  ታራሚዎች የሰብዓዊ የመብት ጥሰት እንዳይፈፀምባቸው እና ጫና እንዳይደርስባቸዉ  ክትትል  እየተደረገ መሆኑን በተሰጠው መግለጫ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...