2ኛው ሀገር አቀፍ የጥበባት ውድድር ሊካሄድ ነው

Date:

“ጥበባት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት!!!” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የጥበባት ውድድር የሚካሄደው ከነሐሴ 28-30 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ሲሆን ውድድሩም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሲካሄድ ሀገር አቀፍ ውድድር የሚያዘጋጀው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ነው።

ይህንን በተመለከተ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙት እና ስለ ሀገር አቀፉ ውድድር ማብራሪያ የሰጡት ረዳት በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ነብዩ (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው።


በዚህም መሰረት ሀገር አቀፉ ውድድር በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በሙዚቃ፣በባህላዊ አልባሳት የፋሽን ውድድር፣ በስነ-ስዕል እና በመነባንብ ውድድሮቹ ይደረጋሉ።

ከላይ በተገለጡት የውድድር ዘርፎች ተስዕጦ ያላቸው ወጣቶች በተለያዩ ክልሎች ውድድሮችን ሲያደርጉ መቆየታቸውንና በውድድሮቹም አሸናፊዎች የሆኑ 364 ባለተስዕጦ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊዎች ይሆናሉ።

በዚህ ውድድር ላይም በየዘርፎቹ ልምድ ያላቸው ዳኞች የሚሳተፉ ሲሆን ለሶስት ቀናት በሚዘልቀው ውድድር ላይ በቅርቡ የሚመረቀውን የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ታሳቢ ያደሪጉ ጥበባዊ ስራዎች በተወዳዳሪዎች አማካኝነት ይቀርባሉ ተብሏል። በዚህ ውድድር ላይ ጥበባዊ ስራዎች ብቻ ለውድድር የሚቀርቡ ሲሆን ክልል ከክልል ወይም ባህል ከባህል ውድድር አይደረግም።

ህብረ-ብሔራዊነት፣የእርስ በእርስ ትውውቅና ኔትዎርኪንግ፣ ልምምድ ልውውጥ ጭምር ይገኝበታል በተባለው ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ አሸናፊ ለሚሆኑ ከፍ ያለ ሽልማትም ይበረከታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፒፕልስ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።


“ሁሉም ልጆች ተስዕጦ እና ራዕይ አላቸው ” በሚል ሀሳብ ለወጣቶች ስልጠናዎችን፣ስኮላር ሺፖችን፣ጥናትና ምርምሮችን፣አውደ ጥናቶችንና ወጣቶች ያላቸውን ተስዕጦ እና ራዕይ በመመርኮዝ በመላው ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።

እ.ኤ.አ በ2021 በጀርመን ሀገር የተመሰረው ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፒፕል በኢትዮጵያም በተመሳሳይ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ስምምነቱን በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረዳት ፕሮፌሰር) እና አቶዘውዱ ገዛኸኝ የሆፕ ፎር ፒፕል ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ተወካይ ናቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የጥበባት ፖሊሲ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...