ትራምፕ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለሀማስ አስተላልፈዋል
ትራምፕ የመጨረሻ ባሉት ማስጠንቀቂያ ታገቾች በፍጥነት ካልተለቀቁ ሁሉም የሃማስ አባል ወደ መቃብር ይወርዳል ሲሉ ዝተዋል
ሃማስ ጋዛን ለቆ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡ እስራኤል በበኩሏ 2025 አመት የጦርነት አመት እንዲሆን መወሰኗን የጦር አዛዡ አስታዉቀዋል፡፡ የጋዛ ህዝቦች ደግሞ የሰብዓዊ እርዳታ ያለህ እያሉ ነዉ፡፡
‹‹ታጋቾችን ነገ ዛሬ ሳትሉ ቶሎ ልቀቁ፡፡በህይዎት ያሉ ታጋቾችን ብቻ ሳይሆን የሟቾችን አስክሬን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል ላኩ ፡፡አለበለዚያ ሃማሶች ሆይ ጊዜዉ እየጨለመባችሁ ነዉ ››ብለዋል
የጋዛ አስተዳዳሪዎች ደግሞ አካባቢዉን ለቀችሁ የምትወጡበት ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡
የጋዛ ህዝብ ሆይ ከፊታችሁ ጥሩ አጋጣሚ ቢኖርም ታጋቸች ካልተለቀቁ ግን ሁሉም ነገር አስከፊ ይሆናል ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸዉ ላይ አስፍረዋል፡፡
ትራምፕ ሃማስን ሲያስፈራሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። በታኅሣሥ ወር፣ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸውን በተረከቡበት ወቅት ታጋቾች ካልተለቀቁ ሀማስ “የሚከፍለው ዋጋ የከፋ ይሆናል” ብለው ነበር ።
ትራምፕ አዲሱን ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት በቅርቡ ተኩስ አቁም ከተፈቱ ታጋቾች ጋር በዋይት ሐውስ ከተገናኙ በኋላ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት አሜሪካ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ከሃማስ ጋር በቀጥታ እየተደራደረች መሆኑን አረጋግጠዋል።
እስራኤል ከንግግሩ በፊት በጉዳዩ ላይ ሀሳቧን መጠየቋን አክለው ተናግረዋል።
ሌቪት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ሕዝብ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ነገር በማድረግ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
የታጋቾች ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አዳም ቦህለር “ለአሜሪካ ሕዝብ ትክክል የሆነውን ለማድረግ በማሰብ የተጀመረ” ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሃማስ እና አሜሪካ “ሁለት ቀጥተኛ ስብሰባዎችን” ከማድረጋቸው በፊት “በርካታ የመረጃ ልውውጦች” መካሄዳቸውን የቢቢሲ የፍልስጤም ምንጭ ተናግሯል።
እስራኤል፤ አሁንም በጋዛ 59 ታጋቾች እንደሚገኙና እስከ 24 የሚደርሱት ታጋቾች በሕይወት እንደሚገኙ ተናግራለች።ከታጋቾቹ መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው እንደሚገኙበት ተገልጿል።
