Date:

32 የወርቅ አምራቾች ፈቃድ ተሰረዘ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የማዕድን ዘርፉ አፈጻጸም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በክልሉ ከሚገኙ 58 ልዩ አነስተኛና 12 ባሕላዊ የወርቅ አምራቾች መካከል አፈጻጸማቸው ደካማ የሆኑት 32ቱ ፈቃዳቸው መሰረዙ ተገለጿል ።

የክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ በስድስት ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት ወርቅ ማምረት ያልቻሉ 12 ልዩ አነስተኛና ሁለት ባሕላዊ አምራቾች አሉ። አሳማኝ ምክንያት ካላቀረቡ በቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።

በድንጋይ ከሰል ማምረት ፍቃድ ከወሰዱ ከ20 በላይ ባለፍቃዶች መካከል፣ እስካሁን ወደ ማምረት የገቡት ስምንት ብቻ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት ታቅዶ 75.525 ኪሎ ግራም፣ እንዲሁም 100 ሺህ ቶን ድንጋይ ከሰል ለማምረት ታቅዶ 50 ሺህ ቶን ብቻ ማምረት መቻሉ ተነገረ ሲሆን የምርት እጥረቱ ምክንያት ሕገወጥነት እና ወደ ሥራ ያልገቡ አምራቾች መኖራቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...