Date:

በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 32 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ

በማይናማር በእገታ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በህንድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በማይናማር በእገታ ሥር ቆይተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያዊያን መካከል፤ 32ቱን ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል ብሏል፡፡

43 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ኤምባሲው ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።

በተያያዘ መንግሥት ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወዳልተፈጸመባቸው ሀገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@አሐዱ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...