3.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

Date:

ሚያዚያ 2፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ክብርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገልጸዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የዳመጠ ሲሆን፤ የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎች አቅርበው ክብርት ሚኒስትሯ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያት ካሚል፣ በግብርናው፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪው ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በሀገር ውስጥና ውጭ ሀገራት ዜጎችን በማሰልጠን እና በማብቃት በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተሰራው ስራ ውጤት ማምጣት መቻሉን ክብርት ሚኒስትሯ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ሀገራዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ሀገራዊ ዕገድትን ለማፋጠን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ክብርት ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተቋሙ የመንግስትን የአገልግሎት ማሻሻያ የሪፎርም ትግበራ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጣራ እንዲሁም ተቋሙ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሰራው ስራ በጥንካሬ አንስተዋል፡፡

ለውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ በይበልጥ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቀጣይ ተኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡

የሥራና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በበይነ መረብ እየሰጠ ያለው አገልግሎት እና የሪፎርም ስራዎች የሚበረታቱ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁሉንም አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ ለዜጎች ፍታሃዊ የሆነ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ፤ ወደ ውጭ ሀገራት የሚሰመሩ ዜጎች ሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላት ዘስገንዝበዋል፡፡

ህግ እና ስርዓትን ተከትለው በማይሰሩ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መውስድ እንዳለበት የምክር ቤት አባላት አስገንዝበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...