የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተማሪዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወሰነ

Date:

የትግራይ ክልል አስተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ ጉዳዩን ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮና ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሌሉበት ሲከታተል የቆየው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም ተከሳሾች የአስተማሪዎችን ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍሉ በመወሰን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ወስኗል። የፍርድ ሂደቱ 1ኛ ተከሳሽ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ 2ኛ ተከሳሽ የትግራይ ፋይናንስ ቢሮ፣ 3ኛ ተከሳሽ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና 4ኛ ተከሳሽ የገንዘብ ሚኒስቴር ባልተገኙበት የተደረገ ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...