የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በዘጠኝ ወራት 5.2 ቢሊዮን ብር ዓረቦን ሰበሰበ

Date:

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአባል የፋይናንስ ተቋማት 5.2 ቢሊዮን ብር ዓረቦን መሰብሰቡን አስታወቀ።

የፈንዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ደሳለኝ አምባው እንደገለጹት ይህ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11.10 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

ከተሰበሰበው ዓረቦን ውስጥ 2.67 ቢሊዮን ብር (51.3%) ከግል ባንኮች፣ 2.47 ቢሊዮን ብር (47.5%) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም 59.49 ሚሊዮን ብር (1.2%) ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት የተገኘ ነው።

በተጨማሪም ከጠቅላላው የፈንዱ ኢንቨስትመንት ውስጥ 11.17 ቢሊዮን ብር (92.24%) በመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት ተደርጓል።

የገንዘብ መድን ፈንድ ስራውን ከጀመረ ሁለት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ነው። ዋና አላማው በባንክና በማይክሮፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ተቀማጭ ገንዘብ ላስቀመጡ ግለሰቦችና ድርጅቶች የመድን ሽፋን መስጠት ነው።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...