አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት “በእሁዱ ውድድር ለመሮጥ ባለኝ ጉጉት ቀን ስቆጥር ነበር ፣ ነገር ግን ልምምድ ላይ በገጠመኝ ጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ውጭ ለመሆን ተገድጃለሁ” ብሏል።
በዓለም ላይ ላሉ አድናቂዎቹ ለድጋፋቸውና ማበረታቻቸውም አመስግኗል።
አሁን ከጉዳት ማገገም ላይ እንደሚያተኩርና በቀጣይ ውድድሮች በተሻለ ብቃት እንደሚመለስ ያለውን ተስፋም አትሌቱ ገልጿል።
በለንደን ማራቶን ለሚሳተፉ አትሌቶች ሁሉ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
