44 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንደሌላቸው ተገለጸ

Date:

“World Population Review” በ2025 ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመጠጥ ውሃ ጥራት ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ነች ብሏል። በዚህም ለኢትዮጵያ 19.2/100 ውጤት ተሰጥቷታል።

ንፁህ ያልሆነን ውሃ ከሚጠጡ 100,000 ሰዎች ውስጥ ምን ያህሉ ዕድሜውን ከውሃው ጋር በተያያዘ እንደሚያጣ መሰረት በማድረግ መለኪያው የተሰራ ሲሆን እንደ ጀርመን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጣልያንና ግሪክ ያሉ ሃገራት 100 ተሰጥቷቸው፥ ዜጎቻቸው ንፁህ ውሃ የሚጠጡባቸው ሀገራት ተብለዋል።

በዝርዝሩ ዝቅተኛው ነጥብ የተሰጣቸው 10 ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ከአኅጉራችን አፍሪካ ናቸው።

ኢትዮጵያ አሁንም 44 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላቸው በዝርዝሩ ሲመላከት ይህም 42.7% ህዝቧን መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ሰዎች ከመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ በሽታዎች የሚጋለጡባትም ነች ተብሏል።

44 ሚሊየን ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አያገኙባትም የተባለችው ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ 60.1 ሚሊየን ህዝብ በመቀጠልም ብዙ ሰዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የማያገኙባት አፍሪካዊ ሀገር ነች።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...