71 ሆቴሎች የእሳት አደጋ መከላከያ ደንብ ሳይሟሉ ደረጃ ተሰጣቸው

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም ዘርፍ ላይ በተደረገ የኦዲት ግኝት፣ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሆቴሎች የግዴታ የእሳት አደጋ መከላከያ ደንቦችን ሳያሟሉ የኮከብ ደረጃ እንደተሰጣቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከተሰጣቸው ሆቴሎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የእሳት አደጋ መከላከያ መስፈርቶችን እንዳላሟሉ ተገልጿል።

​በ2017 ዓ.ም የተካሄደ የኦዲት ግኝት እንደሚያሳየው፣ በደረጃ ምደባ ከተካተቱት 113 ሆቴሎች ውስጥ 71 ያህሉ ከነጭራሹ የእሳት አደጋ መከላከያ የምስክር ወረቀት የላቸውም፡፡

በተጨማሪም፣ ከዚህ ዉስጥ 10 የሚሆኑት ሆቴሎች ዓመታዊ የእሳት አደጋ መከላከያ የምስክር ወረቀት እድሳት ያላደረጉ ናቸው፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት መሠረት፣ በምዘና መመሪያው ውስጥ አስገዳጅ ተብለው የተቀመጡት የእሳት አደጋ መከላከያ መስፈርቶች ሳይሟሉ ደረጃ የመስጠት አሠራር እንዳለ አመልክቷል።

​ይህም ከሆቴሎች የደረጃ ምደባ መመሪያ ጋር የሚቃረን ሲሆን፣ ኦዲቱ ይህ አሠራር መቆም እንዳለበት አሳስቧል። የቱሪዝም ሚኒስቴር አዲስ የተቋቋሙ ሆቴሎች ሥራ ከጀመሩ በአንድ ዓመት ውስጥ መመዘንና ደረጃ ሊሰጣቸው ቢገባም፣ ይህ ተግባር አለመከናወኑ በሪፖርቱ ተጠቁሟል።

​የደረጃ ምደባ ከተከናወነ በኋላ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ አለመደረጉና አንዳንድ ጊዜም እስከ ሁለት ዓመት የሚዘገይ መሆኑ ተገልጿል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...