89ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል ተከበረ

Date:

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር 89ኛውን የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ፊት ለፊት አክብሯል። በበዓሉ ላይ አባትና እናት አርበኞች በመገኘት የአበባ ጉንጉን በማኖር የሰማዕታቱን መስዋዕትነት ዘክረዋል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ ወጣቱ ትውልድ አያትና ቅድመ አያቶቹ ለሀገር ፍቅርና ለአንድነት የከፈሉትን የሕይወት መስዋዕትነት በማሰብ፣ ሀገሩን ከጠላት ጥቃት እንዲጠብቅና ልማቷን እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በየጊዜው በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች ሰላሟን ለማደፍረስና ሕዝቧን አንገት ለማስደፋት የሚደረጉ ሙከራዎችን በልጆቿ ጀግንነት ስታከሽፍ የኖረች፣ በደሟ ታፍራና ተከብራ የቆየች ሀገር መሆኗንም ፕሬዝዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ በነፃነቷ ጸንታ የኖረች ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፣ ዛሬ ደግሞ በልማት አዲስ ታሪክ ለመጻፍ በምታደርገው ጥረት ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...