ኬንያ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት በመጋቢት ወር ማሰራጨት ልትጀምር ነው

Date:

ኬንያ በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመወሰድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ /ከ99 በመቶ በላይ/ መከላከያ የሚሰጠውን አዲስ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት በመጋቢት ወር ላይ ማሰራጨት ትጀምራለች።

በጊሊያድ ሳይንሰስ ኩባንያ የሚመረተው ሌናካፓቪር የተሰኘው መድኃኒት፣ የኤችአይቪ ቫይረስ የመተላለፍ እድልን ከ99.9 በመቶ በላይ ይቀንሳል።

ኬንያ ከግሎባል ፈንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረት የመጀመሪያውን ዙር 21 ሺህ የመድኃኒት መጠን ተረክባለች።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አደን ዱዋሌ፤ የመጀመሪያው ምዕራፍ 15 ግዛቶችን በማካተት በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ይጀምራል ሲሉ ያስታወቁ ሲሆን፤ ተጨማሪ 12 ሺህ የመድኃኒት መጠኖች እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ ይጠበቃሉ ብለዋል።

መድኃኒቱን የማዳረስ ስራው የተጀመረው የአፍሪካ ሀገራት በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስር ከሚደረገው የእርዳታ ቅነሳ ጋር እየታገሉ ባሉበት ወቅት ነው።

በዓለም ዙሪያ ከሚኖሩ 40.8 ሚሊየን ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች መካከል 52 በመቶ የሚሆኑት በምስራቅ እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ናቸው።

አሜሪካ 3.7 በመቶ የኤችአይቪ ስርጭት መጠን ላላት ኬንያ ተጨማሪ 25 ሺህ የመድኃኒት መጠኖችን ለመስጠት ቃል ገብታለች።

በታህሳስ ወር ኬንያ ከአሜሪካ ጋር የ2.5 ቢሊየን ዶላር የሁለትዮሽ የጤና ስምምነት ተፈራርማለች፤ ይህም ትራምፕ USAIDን ካፈረሱ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ስምምነት ነው።

በስምምነቱ መሰረት ዋሽንግተን በአምስት ዓመታት ውስጥ 1.6 ቢሊየን ዶላር የምታቀርብ ሲሆን፤ ኬንያ በበኩሏ 8መቶ50 ሚሊየን ዶላር በማዋጣት ቀስ በቀስ ኃላፊነት ትረከባለች ያለዉ አፍሪካ ኒዉስ ኢንግሊሽ ነዉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...