በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር በቀል ዕውቀቶችን የመለየትና የመሰነድ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለይቶ ለማጥናትና በሥርዓት እንዲሰነዱ ለማድረግ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሰፊ የምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጾአል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና የማኅበረሰብ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰራዊት ሐምዲሶ እንደተናገሩት፣ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ጥንታዊና ጠቃሚ ዕውቀቶች ተለይተው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለልማት እንዲውሉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ እነዚህ ጥናትና ምርምሮች የማኅበረሰቡን ችግሮች በመፍታትና ባህላዊ እሴቶችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል። ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በመለየት ለመሰነድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት የጥናትና ምርምር ግብዓት ወሳኝ መሆኑን ዶክተር ሰራዊት አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ከ40 በላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ሥራቸው በተጨማሪ፣ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የዘርፉ መሪ ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንተው ለእውቀትና ለመረጃ ግብዓትነት እንዲውሉ አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም የሀገርን ተወዳዳሪነትና የውስጥ አቅምን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...