የአብነት ትምህርት ቤቱ በድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ ወደመ !

Date:

በደሴ ከተማ የሚገኘው የስሬ ምንጭ መካነ-ሕይወት መስቀለ ክርስቶስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘ-ጋስጫ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት እና የሰ/ት/ቤት አዳራሽ በትናንትናው ዕለት ምክንያቱ ባልታወቀ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

በቃጠሎውም የአብነት ተማሪዎች መገልገያ መጻሕፍት አልባሳት እና ሌሎች እቃዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰው ሕይወት ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ከ 2,000,000 ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል ።

በደብሩ ከ 200 በላይ የአብነት ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በአሁን ሰአት መጠለያ እና የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያጋጠማቸው በመሆኑ  የአብነት ተማሪዎቹን ለመደገፍ እንዲሁም የወደመውን ሀብት ለመተካት የተቋቋመ ኮሚቴ ስራውን መጀመሩ ተገልጿል ።

ዘጋቢ:- ዲ/ን አዶንያስ ሀብታሙ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...