ከደንብ መተላለፍ  ከ390 ሚሊዮን ብር በላይ በቅጣት ተገኝ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ከተላለፉ ግለሰቦች፣ የግል ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት 397 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ደምብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማዋ የደንብ መተላለፍ 69 ነጥብ ስምንት በመቶ መቀነሱን ገልጸዋል።

ስራ አስኪያጅ ይህን የተናገሩት ትናንት በተካሄደው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም የግምገማና የዉይይት መድረክ ላይ ነው።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያሌው ታደሰ በበኩላቸው በተያዘው አመት በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፍን መቀነስ ቢቻልም አሁንም የደንብ ጥሰቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

አክለውም በከተማችን ጨለማን ተገን በማድረግ እና ቀንም ህገወጥ ግንባታወች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ህገወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታ ካለፉት አመታት አንፃር በተያዘው አመት መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 72 ወንዞችን ከብክለት ለመከላከል ውስጥ ለውስጥ በመሄድ ቆሻሻ የሚለቁ ቱቦዎችን በመለየት ሰፊ ስራ ሰርተናል ብለዋል።

በዚህም በተደረገ ቁጥጥር ከብክለት እንድቆጠቡ የተነገራቸው ተቋማት ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው በተደጋጋሚ መቀጣታቸውን አውስተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...