አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዶ/ር ዳንኤል እንዲፈቱ ጠየቀ

Date:

ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ቀትር ላይ በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና በባህር ዳር ከተማ  በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር የዋሉት የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ከፍተኛ አስተባበሪ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ እንዲፈቱ አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር አውሎ ለእስር የዳረጋቸውን ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በአፋጣኝ” ሊፈታቸው ይገባል ሲል ትላንት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ “የዘፈቀደ እስር አሳስቦኛል” ያለው አምነስቲ “እስሩ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ለህግ የበላይነት ተገዢ ባለመሆን የግለሰቦችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ በነጻነት የመሰብሰብ መብትን ባለማክበር በተደጋጋሚ ህግ እንደሚጥሱ ማሳያ ነው” ሲል ተችቷል።

አምነስቲ በመግለጫው “ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ግለሰቦችን እያሰሩ መክሰስ አሳሳቢ ልማድ ሁኗል” ሲል አስጠንቀቋል፤ እንዲህ ያሉ ድርጊቶች “የህግ የበላይነትን ከመሸርሸራቸው ባለፈ በሀገሪቱ ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ አካሄዶች እንዲለመዱ ያደርጋል” ሲልም አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ እና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሬዚደንት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በአማራ ክል ባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል።

ዶ/ር ዳንኤል ሰኔ 18 ቀን 7፡30 አካባቢ በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን”፣ “ በባህር ዳር ከተማ 13ኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ” ዘገባው አካቷል። “ነገር ግን እዚያ ያሉ ሰዎች እንደነገሩን በማንኛውም ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ሊወስዱት ይችላሉ” ሲሉ ምንጫችን መናገራቸውን ዘገባው ተጠቁሟል።

ዶ/ር ዳንኤል በቁጥጥር ስር የዋለው የጤና ባለሙያዎች የተሻሻለ ክፍያ፣ የተሻለ የስራ ሁኔታ እና ሌሎች ጥያቄዎቻቸው እንዲመለስላቸው ከግንቦት 4 ጀምሮ ሀገራ አቀፍ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

ዶ/ር ዳንኤል በጤና ባለሙያዎች እና በህብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘውን “ዶ/ር ደቦል” የተሰኘ የፌስቡክ ገፅን በመጠቀም በጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ላይ ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

ዶ/ር ዳንኤል መታሰሩ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች “በፖለቲካ ነጋዴዎች ተጠልፏል”  እና ጉዳዩ “ከእንግዲህ በእጃችሁ አይደለም” በማለት ካስጠነቀቁ ከቀናት በኋላ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት “የመፍትሄው መንገድ ከእጀችሁ ተወስዷል” ሲሉ ገልፀው “የአገልግሎት ልምድ የሌላቸው” ጉዳዩን ይዘውታል ብለዋል።

ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ ዶ/ር ማህሌት ጉኡሽ እና የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዮናታን ዳኛውን ጨምሮ ባለሙያውች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ይታወቃል።

ከእስሩ በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች ላደረጉት ስራ የማቆም አድማ ድጋፉን የገለፀው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር በቅርቡ ታግዷል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው በወቅቱ ለአዲስ ስታንዳርድ አንደገለጹት እግዱ የተላለፈው ከኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል ሲሆን እግዱ በዋነኝነት ከጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር የተገናኘ ነው ብለው እንደሚያምኑ” አስታውቀዋል። 

አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...