ታዋቂው ማዲህ ሸህ መሀመድ ሁሴን አረፉ

Date:

ሐገራዊውን “መንዙማ” በዕውቀትና በሥርዓት፣ በተዋበ ድምጽና ወግ በጠበቀ ቅኝት ለትውልድ በማሸጋገር ከ40 ዓመታት በላይ የላቀ ሚና ያበረከቱት ማዲህ ሸህ ሙሐመድ ሑሴን በ63 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት አርፈዋል።

ውልደት እና ዕድገታቸው ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ አካባቢ ነበር። በህይወት ታሪካቻው ላይ እንደተጠቀሰው የዒልም (ዕውቀት)፣ የአዳብ (ሥርዓት)፣ የመንፈሳዊ እነጻ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁት በ“ዛውዮች” በ“ኡላኡላ” በ“መጅት” የዕውቀትና መንፈሳዊ ማዕከላት ነው። በዋነኝነት የዳግማዊ መጅት (ሸህ ሰዒድ ቡሽራ) ምሩቅ ናቸው።

ለመንፈሳዊ መምህራቸው ለዳግማዊ መጅት የላቀ ፍቅር፣ አክብሮትና አገልግሎት (ኺድሚያ) ነበራቸው። ሦስት ጊዜ መካ-መዲና አብሮ የመጓዝ ወርቃማ ዕድል አግኝተዋል። ዱዓ እና ምርቃትም ተችረዋል።

ሸህ ሙሐመድ ሑሴን ለነቢዩ ሙሐመድ ጥልቅ ፍቅር፣ ናፍቆት፣ ተከታይነት ስለነበራቸው ሃያ ለሚጠጉ ጊዜያት ያክል መካ-መዲናን የመመላለሳቸው (መዘየራቸው) ሚስጥር፤ ላለፉት 40 ዓመታት በላይ በመድህ (መወድሰ ነቢ) የማገልገላቸው ምክንያት ከዚያ እንደሚመንጭ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል።

በኢማምነት፣ በመልካም ጸባይ ታግዘው ግብረ ገባዊ ምክርና ታሪክ በመለገስ፣ ሐገርን በጸሎት/ዱዓና እርቅ በማሰብ ይታወቃሉ። በወሎና በአዲስ አበባ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አላቸው። የመንዙማ አበርክቷቸውም በመላ ኢትዮጵያ ዕውቅና አለው።

ከዐስራ አምስት በላይ ዕውቅ ተተኪ ማዲሆችን ያፈሩት ማዲህ ሼህ ሙሃመድ፣ በትዳር ሕይወታቸው የአምስት ልጆች አባት ነበሩ።

ህልፈታቸውን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ሙፍቲ ሐጂ ዑመርን ጨምሮ በርካታ ዓሊሞች (ሊቃውንት)፣ ምሁራንና ምእመናን መንፈሳዊ ሽኝት አድርገውላቸዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም በዛሬው ዕለት በኮምቦልቻ መጂት ሀሪማ ይፈጸማል ተብሏል።

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...