በአዲሱ መመሪያ መሠረት በጉብኝት ቪዛ መደብ ውስጥ የF ፣ M እና J ሁሉም የተማሪ እና የልውውጥ (Exchange) ቪዛ አመልካቾችን የበይነ መረብ (online) አጠቃቀም ጨምሮ ሁሉን አካታች እና ጥልቅ የሆነ ማጣራት እናካሄዳለን።
ይህን የማጣራት ሥራ ለማቀላጠፍ ሁሉም የ F ፣ M እና J ጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ሁሉንም የማህበራዊ ትስስር ገጽ መለያቸውን (Social media profile) ከግል ሴቲንግ (private setting) ወደ ክፍት/ይፋዊ ሴቲንግ (public setting) እንዲያስተካክሉ ይጠየቃሉ ።
