የአውሮፓ ኅብረት በአሜሪካ ምርቶች ላይ ሊጥል የነበረውን የአጸፋ ታሪፍ ለጊዜው አራዘመ

Date:

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሊየን እንዳስታወቁት፣ የአውሮፓ ኅብረት በአሜሪካ ምርቶች ላይ ሊጥል የነበረውን የ21 ቢሊዮን ዩሮ የአጸፋ ታሪፍ ዕቅድ እስከ ነሐሴ መጀመሪያ ድረስ አራዝሟል።

ይህ ውሳኔ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓ ኅብረት ምርቶች ላይ የ30 በመቶ ታሪፍ ከነሐሴ 1 ጀምሮ ለመጣል ማቀዳቸውን በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ የተደረገ ነው።

ትራምፕ የንግድ አጋሮቻቸው በአሜሪካ ምርቶች ላይ የአጸፋ ታሪፍ ከጣሉ የታሪፉን መጠን ከ30 በመቶ በላይ እንደሚያሳድጉ አስጠንቅቀዋል።

ፎን ደር ሊየን ኅብረቱ የመከላከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ እንደሆነ ቢናገሩም፣ ድርድርን እንደሚመርጡ ገልጸው እስከ ነሐሴ 1 ቀን ያለውን ጊዜ ለድርድር እንደሚጠቀሙበት አክለዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት የንግድ ሚኒስትሮች ከዋሽንግተን ጋር በሚኖራቸው ድርድር ምን ዓይነት አቋም መያዝ እንዳለባቸው ተወያይተዋል። የጀርመኑ የገንዘብ ሚኒስትር ላርስ ክሊንግበል ከአሜሪካ ጋር ገንቢ ድርድር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ካልተሳካ ግን ኅብረቱ የራሱን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ የመከላከያ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።

ይህ የሆነው የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአውሮፓ ኮሚሽን የኅብረቱን ጥቅም በቆራጥነት እንዲያስጠብቅ ማሳሰባቸውን ተከትሎ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...