በ2017 በጀት ዓመት 404 ሺህ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች የአፋር ክልልን መጎብኘታቸውን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል።
በክልሉ የመዓድን፣ ፍል ውኃ እና ሌሎችም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን ለማልማት እና የቱሪስት ፍሰቱን ለማሳደግ በተሰሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ትልቅ ለውጥ መገኘቱን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አብዱ መሃመድ ገልፀዋል።
የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ መዳረሻዎችን በማልማት የውጭ እና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረግ መቻሉን አቶ አቡዱ መሃመድ አንስተዋል።
በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት 4 ሺህ 300 የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን የጎበኙ ሲሆን በዚህም 8.6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
በአፋር ክልል የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋትና የዘርፉን እንቅስቃሴ በማጠናከር ረገድ ትልቅ ስኬት እየተመዘገበ መሆኑም አክለው ገልጸዋል።
በቀጣይም ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት በመስጠት በርካታ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን አቶ አብዱ መሃመድ አንስተዋል።
EBC
