“ልሂቃኖቻችን” ያሏቸውን የኦሮሞ ፖለቲካ ተንታኞችን ነቀፉ

Date:


አቶ ሽመልስ ልሂቃኑ ላይ ነቀፋን ያቀረቡት የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) በሳምንቱ መጨረሻ በአዳማ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

በዚህን ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ “ልሂቃን ከሚባሉት አንዳንዶቹ የዶሮ ባህሪ ነው ያላቸው ብለዋል። ሽመልስ፤አንዳንዶቹ ልሂቃን ዶሮ የተሰጣትን እህል አስቀድማ እንደምትበትነው ሁሉ፤ የኦሮሞ ህዝብ ታግሎ አራት ኪሎ ያስገባውን በመበተን ኢንሶሎ፣ ሞያሌ እና ጊዳሚ ማስገባት ይፈልጋሉ” ሲሉ ተችተዋል።


ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ አሁንም እልባት ስላላገኘው የፀጥታ ተግዳሮቶች ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፤ የመንግስታቸው አቋም ከዚህ በፊት ከተቀመጠው አቋም ያልተለየ መሆኑን አስረድተዋል።

“የክልላችን መንግስት የህዝባችንን አንድነት ለመገንባት ያለውን የፖለቲካ ልዩነት በዘመናዊነት መንገድ እንዲመለስ ለማድረግ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ባደረገው ስምምነት ሰፊ ሃይል ገብቷል በየእለቱም እየገባ ነው፤ ለዚህ ትልቅ ክብር አለን፤ አሁንም በዚህ የተከበረ ጨፌ ፊት በቡድን ይሁን በተናጥል እንዲገቡ ዳግም ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

ሽመልስ በመቀጠል የአንድም ሰው ህይወት እንዲጠፋ አንፈልግም፤ ከዚህ ቀደምም እንዳነሳነው ሁሉ የክልላችን መንግስትም ሆነ የፌዴራል መንግስት ከ100 ኪ.ሜ. 99 በመሄድ ለመቀበል ዝግጁ ነን” ብለዋል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...