ፈረንሳይ ለፍልስጤም እውቅና እንደምትሰጥ ገለፀች

Date:



ፈረንሳይ በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግስት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚያደርጉ ከሆነም ፈረንሳይ ይህን በማድረግ የመጀመሪያዋ የG7 ሀገር ትሆናለች ።

ማክሮን በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትክክለኛ መንገድ  በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሚያስፈልገው የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ማድረግ እና ነዋሪዎችን መታደግ ነውም ብለዋል።

እንዲሁም አስቸኳይ የተኩስ አቁም፣ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ እና ለጋዛ ህዝብ ትልቅ ሰብአዊ እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ  ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል።

የፍልስጤም ባለስልጣናት የማክሮንን ውሳኔ የተቀበሉ ሲሆን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ  ግን እርምጃው “ሽብርን ያበረታታል” ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...