የተቃጠለዉ ‎‎ሆስፒታሉ በቀን 700 ታካሚዎች አገልግሎት የሚያገኙበት ነበር

Date:



‎በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በሰዎች ጉዳት ባያደርስም በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

‎የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)፣ “በርካታ ታካሚዎች የተኙባቸው ክፍሎች ስለነበሩ ሠራተኞች በሙሉ ታካሚ ማውጣት ላይ ትኩረት ስላደረጉ በውስጥ የነበሩ በርካታ ንብረቶች ተቃጥለው ወድመዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

‎ሆስፒታሉ በቀን 700 ታካሚዎች አገልግሎት የሚያገኝበት መሆኑን ተገልጿል።‎በመሆኑንም ሆስፒታሉ ወደ ነበረበት እንዲመለስና አገልግሎት እንዲሰጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋራ ድርጅቶች አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጥሪ አቅርበዋል።

‎ከጤና ሚኒስቴር የተወጣጣ ቡድን ዛሬ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት በቦታዉ በመገኘት የተመለከተ ሲሆን የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ ሆስፒታሉን በአጭር ጊዜ አገልግሎት ለማስጀመር ጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ የወላይታ አስተዳዳሪ፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር፣ የጋሞ ዞን  ‎አና ለሎችም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...