በቻይና ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ተሸለመች

Date:

                                  

ጋዜጠኛ ሰላም ተሾመ ከሰሞኑ በቻይና በተካሄደው የ”Road and Belt journalist forum” ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ተገኝታ ነበር።

ይህ ፎረም ለ 7ቀናት የቆየ ሲሆን ጋዜጠኛ ሰላም በዕለቱ ባደረገችው ከመንገድ ጋር የተያያዘ ንግግር ከፍተኛ አድናቆትን አትርፋለች፡፡ ጋዜጠኛዋ ሀሳቦችን በቁጥር  ከመግለፅ ይልቅ ሰው ላይ ትኩረትን ያደረገ ሀሣብ በማቅረቧ በፎረሙ ተሳታፊዎች ዘንድ ለመደነቅ ችላለች፡፡

ጋዜጠኛ ሰላም ለተወዳጅ ሚድያ እንደተናገረችው ይህ ሥራዋ የአገሯን ስም እንድታስጠራ ያስቻላት መሆኑን ተሸላሚም እንዳደረጋት ገልፃለች።

“The Belt and Road Journalists Forum” በየዓመቱ የሚደረግ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚያገለግሉ የሙያ ማህበራት የሚሳተፉበት ጉባዔ ነው፡፡

ጉባዔው በ All China Journalists Association የሚዘጋጅ ሲሆን ዘንድሮ ለ ሰባተኛ ጊዜ በቻይና ጃንጉ ተደርጎል።

ከ 50 ሀገራት የተወጣጡ 100 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።  በመድረኩ ፦8ላይ  ከቤልት ኤንድ ሮድ ጋር እና ከጋዜጠኝነት ሙያ ጋር በተገናኘ ልምዳቸውን በንግግር ከገለጹ 8 ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች መካከል ሰላም ተሾመ አንዷ ነበረች።

በንግግሯም፣ ከቁጥራዊ ዘገባ ይልቅ የሰዎችን ሕይወት ተስፋዎችን እና ለውጦች እንዲሁም ፈተናዎችን በዘገባችን ማሳየት ይገባናል ብላለች።

ሙያቸውን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ፣ቻይና፣ሰርቢያ ብራዚል እና የካምቦዲያ ጋዜጠኞች የ 2025 Belt and Road Journalists Forum የሚዲያ አምባሳደር ተደርገው እውቅና
ተሰጥቷቸዋል።

በዚህ ጉባዔ ላይ በኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር ፕሮዲዩስ የተደረገ አጭር ዘጋቢ ፊልም ምርጥ 10 ውስጥ በመግባት እውቅና አግኝቷል።ለአጭር ዘገባ ፊልሙ ውድድር 100 በላይ ፊልሞች ቀርበው ነበር።

ሰላም ተሾመ፣ ላለፉት 12 ዓመታት በተለያዩ ሚዲያዎች ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ሠርታለች፡፡ በዛሚ፣ፋና፣ኤል ቲቪ በሪፖርተርነት
በአሀዱ ቴሌቪዥን ዜና ክፍል፣በዋዜማ ሬዲዮ በዋና አዘጋጅነት በያ ቲቪ በምክትል ሥራ አስኪያጅ እና አማካሪነት በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን የዲጂታል ክፍል ዳይሬክተር አሁን ደግሞ በፋና ቴሌቪዥን የመዝናኛ ክፍል ዋናአዘጋጅነት እና በፋና ማሰልጠኛ ደግሞ አሰልጣኝ ሆና እያገለገለች ትገኛለች።

ሰላም ተሾመ፣የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዋን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጆርናሊዝም እና ኮምዩኒኬሽን አግኝታለች።ከ IMS,DW Akademie, CFI  እንዲሁም Code for Africa ሥልጠናዎችን በመውሰድ ሰርቲፋይ ሆናለች።

ዘገባ ዕዝራ እጅጉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...