የካቲት 12 ሆስፒታል ከ37ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህሙማን የድንገተኛ  ህክምና መስጠቱን አስታወቀ

Date:

ባለፈዉ የ2017  በጀት ዓመት የካቲት 12 ሆስፒታል ከ 37 ሺ  በላይ ለሚሆኑ ህሙማን የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል።

በሆስፒታሉ የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃላፊ ዶ/ር ሞላልኝ ውብአንተ የድንገተኛ ጊዜ ህክምና የህፃናትን ፣የማህፀን እና ፅንስ እንዲሁም የአዋቂዎችን የድንገተኛ ህክምና ያጠቃልላል ያሉ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 15ሺ 600 የሚሆነው ህክምና የተሰጠው ለአዋቂዎች ነው ብለዋል።

ሃላፊው በአንድ ወር ውስጥ ከ1ሺህ 3መቶ በላይ አዋቂዎች ከቃጠሎ፣የመኪና አደጋ እንዲሁም ትሯማ ጋር ተያይዞ በድንገተኛ አደጋ ወደ ሆስፒታሉ ይመጣሉ ሲሉ ተናግረዋል ።

ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ አካባቢዎች በሪፈር ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታሉ በተለይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእሳት ቃጠሎ ህክምና  እንደሚታወቅም ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ ለምግብ ማብሰያነት አገልግሎት የሚውሉ ጋዞች ፍንድተው ለሴቶች እና ህጻናት የቃጠሎ አደጋ ተጋላጭ የማህብረተሰብ ክፍሎች ሆነው መለየታቸውን ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...