ኩላሊቴን መልሽ ወይም 1.5 ሚሊዮን ዶላር ክፈይአነጋጋሪው የፍች ጥያቄ

Date:



በኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ በተከሰተ የፍቺ ሂደት ውስጥ ያልተለመደ እና አነጋጋሪ ክስተት ተፈጠረ።

ዶ/ር ሪቻርድ ባቲስታ የተባሉ አንድ ሰው፣ ለባለቤታቸው ከዓመታት በፊት የለገሱትን ኩላሊት እንዲመልሱላቸው ወይም በምትኩ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ በይፋ መጠየቃቸው እየተዘገበ ነው።

ይህ ጥያቄ በህጋዊ መንገድ የጸና ባይሆንም፣ ጉዳዩ ከፍተኛ የህዝብ ክርክር የቀሰቀሰ ሲሆን፣ በግንኙነቶች ውስጥ ስለሚደረጉ የግል መስዋዕትነቶች ስሜታዊ ክብደት ሰፊ ውይይት እንዲነሳ አድርጓል ነው የተባለው።

የዶ/ር ባቲስታ ጥያቄ፣ ትዳር ሲፈርስ፣ ህይወት አድን የሆኑ ስጦታዎች እንኳን የሚያሰቃይ የክርክር ነጥብ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጎላ አድርጎ አሳይቷል ነው የተባለው።

ይህ ክስተት በፍቅር እና በመስዋዕትነት ስም የተሰጡ ነገሮች፣ ግንኙነቶች ሲሻክሩ ሊፈጠሩ የሚችሉ ውስብስብ ሁኔታዎችን ያሳያል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...