አርባምንጭ በተፈጥሮ ስሪቷ ውብ ናት

Date:

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት በከተማዋ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎች በቅርቡ በጎበኘንበት ወቅት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ተመልክተናል። ይኽ ሥራ በመጠነ ርዕዩ ግዙፍ በመሆኑ አርባምንጭ ታላላቅ ጉባኤዎችን እንድታስተናገድ ያስችላታል።

ከዚህ ቀደም ከነበረን ምልከታ ሰፋ ብሎ የተከናወነው የኩልፎ ወንዝ ዳርቻ ልማት ለከተማዋ ልዩ መልኮች ተጨማሪ ገጽታ ፈጥሯል።

ወደ አርባምንጭ ጫካ አዳዲስ የመግቢያ መንገዶች የተሠሩ ሲሆን ለተራሮቹ፣ ለውሃውና ለከባቢው ደኖች መዳረሻ በር ሆነዋል።

እነዚህና ሌሎች ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ብዙ ከተሞች ያየናቸው መሻሻሎች የተለያዩ አማራጮች እንዳሉን የሚያሳዩ ያልተጠቀምንባቸውን አቅሞቻችንንም የሚገልጡ ናቸው። ይኽ እድገት በጋራ ጥረቶቻችን ታላላቅ ነገሮችን እንደምናሳካ የሚያመለክት ግልጽ ምልክት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...