መንግስት 70 በመቶ ክፍያውን የሚሸፍነው የእንስሳት ኢንሹራንስ

Date:

በእንስሳት ኢንሹራንስ  ከ189 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች አባል ሆነዋል፡፡

የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የአደጋ  ስጋት ተጋላጭነት ለመቀነስ የእንስሳት ኢንሹራንስ ፖሊሲው ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር ነው ያስታወቀው።

በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ ስጋት ቅነሳና የአርብቶ አደር አካታች የኢኮኖሚ ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ አቶ ጀማል አሊይ  እንዳሉት የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

ከዚህ ውስጥ የእንስሳት ኢንሹራንስ ፖሊሲ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ፖሊሲው የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።

የአደጋ ስጋት ቅነሳና የአርብቶ አደር አካታች የኢኮኖሚ ፕሮጀክት በኦሮሚያ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ድርቅ ሲያጋጥም እንስሳቱ ሳይጎዱ ወደ ጥሬ ገንዘብ የሚለወጡበት አሰራር የሚተገበርበት መሆኑን ተናግረው በእንሰሳት ኢንሹራንሱ መሰረትም መኖ፣ ውሃና መድሃኒት ለእንሳሳት እንደሚገዛም ገልጸዋል።

የኢንሹራንስ ክፍያውም 70 በመቶ በመንግሥት የሚሸፈን ሲሆን ቀሪ 30 በመቶ በአርብቶ አደሩ እንደሚከፈል ተናግረዋል።

በዚህም ከ189 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች የኢንሹራንሱ አባል መሆን ችለዋል።

KGEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...