በስዊድን ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ሁኔታ እየተጓጓዘች ነው

Date:

ስዊድናውያን ጥንታዊ ቤተክርስቲያናቸውን ከነበረችበት ስፍራ ሙሉ ይዘቷን እንደጠበቀች በማንሳት ወደ ሌላ ስፍራ አጓጉዘዋታል።

ወደ 113 ዓመት እድሜ እንዳላት የተነገረላት የኪሩና ቤተክርስቲያን
ሙሉ በሙሉ በእንጨት የተሰራች እና የሀገሪቱ ጥንታዊ የሥነ ህንጻ ጥበብ ማሳያም ተደርጋ ትቆጠራለች።

ቤተ ክርስቲያኗ የተገነባችበት ስፍራ ቀደም ባለው ጊዜ የማዕድንቁፋሮ ይካሄድበት የነበረ በመሆኑ አሁን ላይ አካባቢው የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሞታል።

ይህን ተከትሎም ቤተ ክርስቲያኗን በከባድ ማሽን በታገዘ የጭነት ተሽከርካሪ ወደ ሌላ ስፍራ እየተጓጓዘች ሲሆን፥ የቤተ
ክርስቲያኗ ይዞታ ባለበት እንዲደርስ በሠአት 500 ሜትር ፍጥነት እንዲጓዝ ተደርጓል።

ቤተክርስቲያኗ 35 ሜትር ከፍታ እና 40 ሜትር ስፋት ያላት ሲሆን፥ አጠቃላይ ክብደቷ672 ሺህ ኪሎ ግራም ትመዝናለች ነው የተባለው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ቤተ ክርስቲያኗ በመጨረሻም ከአንድ ሠአት በፊት በተዘጋጀላት አዲስ ስፍራ ደርሳለች።

(አራዳ ኤፍ ኤም)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...