የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ማህበር ዋና ፕሬዝዳት ሾመ

Date:

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዳሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ማህበር ዋና ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ተገልጿል።

“የትምህርት ምዘናን ለማሸጋገር ጥራት ያለው ትምህርትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 41ኛው የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ተጠናቋል።

በዚህም የጉባዔ የመዝጊያ ፕሮግራ ላይ የኢትዮጵያ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የአፍሪካ ትምህርት ምዘና ማህበር የወቅቱ ፕሬዝዳንት በመሆን ሹመታቸውን ተቀብለዋል።

ኢትዮጵያ የማህበሩ አባል በመሆን በተለያዩ በማህበሩ ጉባዔዎች ላይ ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፤ በዘንድሮው ዓመት 41ኛው የማህበር ዓመታዊ ጉባኤ በመዲናዋ አዲስ አበባ እንድካሄድ ተደርጓል።

በመሆኑም ጉባኤው በአዲስ አበባ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ከ30 በላይ የማህበሩ አባል የሆኑ የአፍሪካ ሀገሮችና ከ20 በላይ ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ የማህበሩ አጋሮች በተገኙበት ሲካሔድ ቆይቷል፡፡

ጉባኤው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተልዕኮውን በላቀ ውጤታማነት ለመወጣት ያግዘው ዘንድ ከተለያዩ ተሳታፊ ሀገራት እውቀት፣ ልምድ፣ ቴክኖሎጂና ሌሎች መልካም ተሞክሮዎችን ለመቅሰም እና ለመጋራት ምቹ መድረክ እንደነበር፤ የትምህርትና ምዘና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በጉባዔው በትምህርትና ምዘናና ስርዓት ዙሪያ ያሉ እሳቤዎች፣ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ልምዶች መቅረባቸውን አንስተው፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣት ጠንካራ መሆንን የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

የጉባዔው ዋና አላማ በምዘናና ፈተና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ፤ ዘላቂ የሆነ ትብብርን በመፍጠር በጋራ ለመስራት መሆኑን አንስተዋል።

በጉባዔው ማብቂያ ላይም 42ኛውን የአፍሪካ ትምህርት ምዘና ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ታንዛኒያ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...