ቴሕራን-ኢራን ከኑክሌር አጋጁ ሥምምነት የሚያስወጣ ደንብ ልታረቅ ነዉ

Date:

የኢራን ብሔራዊ ምክር ቤት (ፓርላማ) ሐገሪቱ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይመረት ከሚያግደዉ ዓለም አቀፍ ሥምምነት እንድትወጣ የሚያደርግ ሕግ እንደሚያረቅ አስታወቀ።

ኢራን እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2015 የተደረገዉን ሥምምነት «አላከበረችም» የሚሉት ጀርመን፣ፈ,ረንሳይና ብሪታንያ በኢራን ላይ ከዚሕ ቀደም ተነስቶላት የነበረዉ ማዕቀብ ዳግም እንዲጣልባት ጠይቀዋል።

የኢራንን የኑክሌር መርሐ ግብር ያስቆመዉንና የተጣለባትን ማዕቀብ ያስነሳዉን ሥምምነት ከቴሕራን ጋር የተፈራረሙት በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉ አምስቱ ሐገራት፣ ጀርመንና የአዉሮጳ ሕብረት ናቸዉ።

ይሁንና የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2018 ሥምምነቱን ሲያፈርሱ ሌሎቹ የስምምነቱ ፈራሚዎች ያሉት ነገር አልነበረም።

ኢራን በእስራኤልና በዩናይቴድ ስቴትስ ከተደበደበች በኋላ የኑክሌር ተቋማቷን በዓለም አዉቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት ባለሙያዎች ለማስፈተሽ ሥታንገራግር ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዳግም በማዕቀብ እንዲጥልባት 3 መንግሥታት ጠይቀዋል።

ኢራን ጠንካራ አፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ስታስጠነቀቅ፣ ሩሲያና ቻይና የሶስቱን ሐገራት አቋም አጥብቀዉ ተቃዉመዉታል።

የኢራን ምክር ቤት ደግሞ ቴሕራን ኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይመረት ከሚያግደዉ ዓለም አቀፍ ሥምምነት ጨርሶ እንድትወጣ የሚያደርግ ሕግ ለማርቀቅ መዘጋጀቱን አስታዉቋል።

የጀርመኑ ዜና አገልግሎት DPA ዛሬ እንደዘገበዉ ምክር ቤቱ ደንቡን ለማርቀቅ መዘጋጀቱን አንድ የምክር ቤቱ ባለሥልጣን አረጋግጠዋል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...