በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለውና በ300 ካሬ ሜትር ላይ በዘመናዊ መልክ አገልግሎት የሚሰጠው ጃፋር የመጻሕፍት መደብር (Jafar Book Store) ባህልና ስፖርት ሚንስትር ዲኤታ የሆኑት ረ/ፕ ነብዩ ባዬ ቅዳሜ ነሐሴ 24 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።
በለገሐር በተወልደ ህንፃ ላይ አገልግሎት መስጠት የጀመረው (Jafar Book Store)የምርቃት ፕሮግራም ላይ የእለቱ የክብር እንግዳ በሆኑት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ እና የስታትስቲክ ባለሙያውና ወግ አዋቂው በኃይሉ ገ/መድህን ጃፋር ላለፉት 25 ዓመት በመፅሐፍ ህትመትና ስርጭት ላይ ያበረከተውን አስተዋፅዖ አድንቀዋል።
እንዲሁም ይህን ግዙፍ የመጻሕፍት መደብር መክፈቱ ለመፅሐፍ ወዳጆች ለደራሲያንና ለአንባቢያን ልዩ ትርጉም ያለው እንደሆነ ተናግረው አመስግነውታል:: በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ በርካታ ደራሲያን የኪነጥበብ ባለሙያዎች አንባቢያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::
አገልግሎት መስጠት የጀመረው (Jafar Book Store) የደህንነት ካሜራ የተገጠመለት ሲሆን መፅሐፍ ለመግዛት ወደ መደብሩ የሚመጣ ሰው ልክ እንደ ሱፐር ማርኬት የሚፈልገውን መፅሐፍት በአይነታቸው ከተደረደሩበት ሼልፍ ላይ እያነሳ በዘንቢል በመያዝ መርጦ ከጨረሰ በኋላ ግብይቱ የሚካሄደው በዲጂታል ቴክኖሎጂ መፅሐፉ ላይ ያለውን ባር ኮድ እስካን በማድረግ ግብይቱን ፈፅሞ ይወጣል ::
በ1992 ዓ.ም ወደ መፅሐፍ ንግድ የገባው ጃፋር ሺፋ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት መፅሐፍን በማሳተም በመሸጥና በማከፋፈል የስራ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ በርካታ የመፅሐፍ መደብሮቹ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::
(ይትባረክ ዋለልኝ)
