ግብፅ ከሰሞኑ በርካታ ህፃናት ቲክቶከሮች እያሰረች ነው

Date:

የግብፅ አስተዳደር በሚሊየን የሚቆጠሩ ተከታይ ያላቸውን ህፃናት ቲክቶከሮች እሴትን ከመሸርሸር እስከ ገንዘብ ማጭበርበር ድረስ እየከሰሰ እያሰረ ነው ተብሏል።

ፖሊስ ያልተገባ የገንዘብ ጥቅም አግኝተዋል ያላቸውን ቢያንስ 10 ጉዳዮች እየመረመረ መሆኑን እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን መያዙን ተጠርጣሪዎች ገንዘባቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ማድረጉን እንደዚሁም የጉዞ እግድ መጣሉን ገልጿል።

የማህበራዊ ሚዲያው በግብፅ መንግስት በበላይነት ለተያዘው የተለመደው የሚዲያ ዘርፍ አማራጭ ሆኖ ብቅ ያለ ሲሆን ጠበቆች ፖሊስ በቀላሉ የቲክቶከሮቹን ልጥፎች በማየት ገቢው ትክክለኛ መሆኑን ማጣራት ይችል ነበር ብለዋል።

ማሪያም አይማን የተባለች 9.4 ሚሊየን ተከታይ ያላት የ19 አመት ቲክቶከር ከነሐሴ 2 ጀምራ እስር ላይ ስትሆን ተገቢ ያልሆነ ይዘት በማሰራጨት እና 15 ሚሊየን የግብፅ ፓውንድ በማጭበርበር ተከሳለች።

ልጅቷ ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶችን ማጋራቷን ተከትሎ ቅሬታ ስለቀረበ መታሰሯን የግብፅ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲገልፅ ልጅቷ በመጨረሻዋ ቪዲዮ ” ግብፃዊያን በቲክቶክ ስለቀረቡ ብቻ አይታሰሩም” ማለቷ ተዘግቧል።

በግብፅ የሳይበር ህግ የማህበረሰቡን እሴት የሚሸረሽሩ ይዘቶችን ማጋራት በወንጀልነት ሲቀመጥ ባለሙያዎች ግን የተቀመጠው ህግ ግልፅ አይደለም ብለዋል።

ሌላ እንደዚሁ ሱዚ የተባለች ቲክቶከርም ስትታሰር ከእስሯ በፊት በተቀረፀ ፖድካስት ላይ 10 ሚሊየን የግብፅ ፓውንድ ብታገኝ ግማሹን ቤተሰቦቿን የተሻለ ኑሮ ለማኖር እንደምትጠቀም ስትገልፅ ፖድካስቱን የለቀቀው ግለሰብም ከእሷ በኋላ ታስሯል ተብሏል።

የግብፅ የቤተሰብ እሴትን ጥሰዋል በሚል በርካታ ቲክቶከሮች ሲታሰሩ ባለፉት አምስት አመታት ቢያንስ 151 ሰዎች በዚህ ጉዳይ መከሰሳቸው ተገልጿል።

ግብፅ በተደጋጋሚ ቲክቶከሮች ቪዲዮ ሲሰሩ የማህበረሰቡን እሴት እንዲጠብቁ ስታስጠነቅቅ ጠበቆች አንዳንዶቹ የታሰሩት ባልተለቀቀ የግል ቪዲዮ ነው ብለዋል።

ቲክቶክ እራሱ ከገፁ 2.9 ሚሊየን የግብፅ ቪዲዮዎችን ማጥፋቱን ገልጿል።

የማህበራዊ ሚዲያ አማካሪ ራሚ አብድልአዚዚ በ1000 እይታ የግብፅ ቲክቶከሮች በአማካይ 1.2 ዶላር እንደሚያገኙ አንስቶ ብዙ ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ለማግኘት ረጅም ጊዜን ይወስዳል ብሏል።

መንግስት ጉዳዩ የገንዘብ ማጭበርበር ከሆነ ድርጅቶችን እንጂ የይዘት ፈጣሪዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሌለበትም የፋይናንስ ባለሙያዎች መክረዋል።

የሰብዓዊ መብት ተቋማት ግን ህጎቹ ግልፅ አይደሉም ያሉ ሲሆን እየተተገበረ ያለውም በዘፈቀደ ነው ሲሉ ኮንነዋል።

Source: Reuters

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...