የዓረብ ሊግ ስለ ሕዳሴ ግድብ

Date:

የዓረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አስተዳደር ዙሪያ ባስቸኳይ አስገዳጅ የሦስትዮሽ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ካይሮ ውስጥ ከተሰበሰቡ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ አሳስበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ፣ ስምምነቱ የግብጽንና ሱዳንን የውሃ ደኅንነት የሚያረጋግጥ መኾን እንዳለበትም ገልጸዋል።

የግብጽና ሱዳንን የውሃ መብት የሚጥስ ማናቸውንም የተናጥል ርምጃ ውድቅ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ፣ አስገዳጁ የሦስትዮሽ ስምምነት የኹለቱን አገራት የውሃ ደኅንነት የሚያረጋግጥ መኾን አለበት በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል።

ዓረብ ሊግ ሕዳሴ ግድብን ወደፊትም መወያያ አጀንዳው አድርጎ እንደሚቀጥልም ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ አስታውቀዋል።

[ዋዜማ]

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...