በኢትዮጵያ የፈረንሣይ አምባሳደር ስለ ፍልስጤም የሃገርነት ዕውቅና ምን አሉ?

Date:

ፈረንሣይ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በይፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ስትሰጥ፣ “በ1967ቱ ሦስተኛው የአረብ-እስራኤል ጦርነት ወቅት በወረራ የተያዙባትን አካባቢዎች ያካተተ እንደሚሆን” በኢትዮጵያ የፈረንሣይ አምባሳደር አሌክሲስ ሌመክ ተናገሩ።

አምባሳደሩ ይሄን ያስታወቁት የፍልስጤም አገርነት እውቅናን በተመለከተ የፈረንሣይ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራርያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አሌክሲስ ሌመክ በዚሁ ወቅት “ዛሬ የምናየው ፈረንሣይ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና መስጠቷ፤ ከዘጠኝ ወራት በፊት በጎርጎሮሳውያኑ 2024 መጨረሻ ፈረንሣይ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር በመሆን የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭትን ለመቋጨት የሁለት ሀገርነትን መፍትሄ ለመጀመር የታለመ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ፈረንሣይ ከስምንት አስርት ዓመታት በላይ የእስራኤል ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱን ስትደግፍ ቆይታለች” ያሉት አምባሣደሩ፤ “ገና ከጅምሩ እስራኤል መሬት እንዲኖራት፣ መንግሥት እንድትመሰርት በመደገፍና የእስራኤል ህልውና አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት ሳይቀር ከእስራኤል ህዝብ ጎን መሰለፏን” አስታውሰዋል።

አክለውም፤ “የፍልስጤም ህዝብ በተመሣሣይ አንድ አይነት መብት እንዳለውና ተመሳሳይ ህግም በነሱ [በፍልስጤማውያን] ላይ መተግበር እንዳለበት እናምናለን” ሲሉ ገልፀው፤ ለእስራኤልና ፍልስጤም የሰላም ሂደት ብቸኛው መፍትሄ “የሁለት ሀገርነት መፍትሔ ነው” ብለዋል።

ይህም ፍልስጤማውያንና እስራኤላውያን ሁለት ሀገራት ሆነው በሰላምና በፀጥታ አብረው የሚኖሩበት መፍትሔ ነው ሲሉም  አስረድተዋል።

በተጨማሪም 148 የሚሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና መስጠታቸውን ጠቅሰው፤ “ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና መስጠት መጨረሻው አይደለም፤ ይልቁንም የሂደቱ መጀመሪያ ነው። ሂደቱም ቀድሞውኑ ተጀምሯል” ሲሉ ተናግረዋል።

አስ-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...