የአሜሪካ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘጉ

Date:

የአሜሪካ መንግስት የፌደራል መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ። የአሁኑ የመስሪያ ቤቶች መዘጋት ስራ ማስኬጃ ገንዘብ ለመበጀት የተቀመጠው ሴኔት በውሳኔ ሃሳብ መስማማት አለመቻሉን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

ከፈረንጆቹ 2018 ወዲህ የመጀመሪያ የሆነው አጋጣሚ የተወሰኑ የአሜሪካ የመንግስት አገልግሎቶችን በጊዜያዊነትም ቢሆን ሊያቋርጥ ይችላል መባሉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ቀደም ብሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመስሪያ ቤቶቹ መዘጋት የሚቀጥል ከሆነ በርካታ ሰራተኞች እስከ ወዲያኛው ሊሰናበቱ ይችላሉ ሲሉ ማስጠንቀቃቸውንም ዘገባው አስታውሷል።

አሁን ላይ የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ በጣም አስፈላጊ ሰራተኞች ብቻ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ሲገለጽ፥ ከዚህ ውስጥ የተወሰኑት ያለ ክፍያ ይሰራሉ ነው የተባለው።

አብዛኛዎቹ የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ያለ ክፍያ ዓመታዊ ዕረፍት እንዲወጡ እንደሚደረግም ዘገባው አመላክቷል።

የመስሪያ ቤቶቹ መዘጋት በዓለም አቀፉ ገበያ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩንም ዘገባው ጠቅሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...