የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Date:

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በቢሮአቸው ውስጥ ያለ ምንጭ ጠቅሶ ሮይተርስ ዛሬ ጠዋት ዘግቧል።

እስካሁን ተጨማሪ ዝርዝር ነገር አልተገለጸም።

በደቡብ ህንድ ኮቺ ከተማ ህክምና ሲከታተሉ የነበሩት ኦዲንጋ ዛሬ በልብ ድካም ምክንያት  ህይወታቸው ማለፉን ተዘግቧል።

አንጋፋ ተቃዋሚ መሪ የሆኑት ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዝዳንትነት አምስት ጊዜ ቢወዳደሩም አላሸነፉም። ከእነዚህ ምርጫዎች ውስጥ ሁለቱ — በፈረንጆቹ 2007 እና በ2017 የተደረጉት — ብጥብጥን በመቀስቀስ በአገሪቱ ውስጥ ወደ ሁከት እና ጥልቅ ክፍፍል አምርተዋል።

ኦዲንጋ በኬንያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ውስጥ ባላቸው ሚና በሰፊው ይታወቃሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...